Head of Office
Chief Executive
Competency and Human Resource Management Executive
Strategic Affairs Executive
Finance and Procurement Executive
Information and Communication Technology Executive
Audit Executive
Basic Services Executive
Public Relations and Communication Executive
Ethics and Anti-Corruption Executive
Women and Social Affairs Executive
Performance and Human Registration Management Executive
Organizational Change Executive
Legal Service Executive
Livestock Product Regulatory Lead Executive
Livestock Quarantine Regulatory Lead Executive
Agricultural Research Extensions and Mechanization Regulatory Lead Executive
Plant Input and Plant Product Testing Laboratory Lead Executive
Pesticides and Fertilizer Regulatory Lead Executive
- የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ፍቱንነት፣ጥራት እና ደህንነትን በመስክ ፣በላቦራቶሪ እና በዶሴ ግምገማ በማረጋገጥ ፀረ-ተባይን እና ማዳበሪያን በሀገር-አቀፍ ደረጃ ይመዘግባል፤
- ፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ከተመዘገበ በኋላ የቅድመ-የማስገቢያ ፈቃድ እንዲሁም ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ የመልቀቂያ ፈቃድን ይሰጣል፣መስፈርቱን ካላሟላ ደግሞ እንዳይገባ ያግዳል፣ ወይም እርምት እንዲደረግበት ወይም ወደ መጣበት ሃገር እንዲመለስ ያደርጋል፣ይህንን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- ፀረ-ተባይና ማዳበሪያን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን፤ በሃገር ውስጥ ከአንድ ክልል በላይ ለሚደረግ ማምረትን ወይም ማዘጋጀትን፤ እንደገና ማሸግን፤ ማከፋፈልን፤ማጓጓዝን፣ ርጭት አገልግሎትን፣ ማስወገድን፣ የማጠንት አገልግሎትን በሚመለከት መስፈርት አዘጋጅቶ ለተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣ በተቋማቱ ላይ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ እንዲታደስ፣እንዲሰረዝ ወይንም እንዲታገድ ያደርጋል፤
- ፀረ-ተባይ ወይንም የማዳበሪያ የድህረ-ምዝገባ የመስክ ፍቱንነት፣ የላቦራቶሪ የኬሚካል ቅሪት ወይም የላቦራቶሪ ጥራትን ያረጋግጣል ወይንም ለማረጋገጥ አግባብነት ላለው ተቋም ለምርምር/ምርመራ/ናሙና እንዲላክ ያደርጋል፤በውጤቱም ላይ በመስረት አስፈላጊውን የሬጉላቶሪ እርምጃ ይወስዳል፤
- የፀደቁ ህጎችን በሚፃረር ሁኔታ ሀገር ውስጥ ገብቷል ወይንም ጥቅም ላይ ውሏል ብሎ ያመነበትን ፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ወይም ለማስረጃነት ይጠቅማል ያለውን ማንኛውም ሠነድ/መረጃ እንዲያዝ ያደርጋል፣ ጉዳዩን ይከታተላል፣ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፤
- በፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ምክንያት በአካባቢ፣ በሰው ፣እንስሳት ወይም በዕፅዋት ላይ የቶክሲኮሎጂ ተጽዕኖ የደረሰ እንደሆነ ወይንም እየደረሰ መሆኑ ከተጠረጠረ መንስኤውን ለመለየት ሀገር-አቀፍ ክትትል ያደርጋል ፣የክትትል ውጤቱን መሠረት በማድረግ ተገቢውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
- ፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ የመስክ ፍቱንነት ሙከራ ባግባቡ መካሄዱን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ ሲሆን ሙከራው እንዲታገድ ፣እንዲቆም ወይንም እንዲሰረዝ ያደርጋል፡፡
- የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያን በሚመለከት የድህረ-ምዝገባ ሀገር-አቀፍ የፍቱንነት፣ የጥራት እና የደህንትን የክትትል ያደርጋል ፣ በተሰበሰቡ መረጃዎችን በመንተራስ ፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያን ዳግም ይመዘግባል ፣ ከምዝገባ ያግዳል ፣የምዝገባ ገደብ ያረጋል ወይም ምዝገባን ይሰርዛል፤
- የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ተቋማት ብቃት አሰጣጥ፣ እንዲሁም ከ የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ምዝገባ እና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ መስፈርት ያዘጋጃል፣ የሕግ ማዕቀፎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤ የነበሩት ሕጎች እንዲሻሻሉ፣ አስፈላጊ ሲሆንም አዳዲስ የሕግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ የሕግ ማዕቀፎቹ ሲዘጋጁ በንቃት ይሳተፋል እና ሲጸድቁም አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ፣ይቆጣጠራል፤
- በሀገሪቱ የመግቢያና መዉጫ በሮች ፣ ደረቅ ወደቦች ላይ የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ኢንስፔክሸን ስራን ያከናውናል ፣ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- ከፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ምዝገባ ጋር የተያያዙ የጥራት፣ፍቱንነት፣ደህንነት ጋር ተያያዥ የሆኑ ስታንዳርዶችን እና ፕሮቶኮሎች ተግባራዊ ያደርጋል፣ እንደ አስፈላጊነቱም ያሉት ስታንዳርዶች እና ፕሮቶኮሎች እንዲሻሻሉ ያደርጋል፣ አዳዲስ ስታንዳርዶች ከኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢንሲቲትዩት ጋር በመተባበር ያወጣል፣ የተሻሻሉ ወይንም አዳዲስ ስታንደርዶችን እና ፕሮቶኮሎች ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በአሀጉር ወይም በዓለምአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የሌሎች አገሮች፣ የጋራ ስምምነቶች እና ሌሎች የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ ዘዴዎችን ተቀብሎ አንደ አስፈላጊነቱ ተግባራዊ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል ይቆጣጠራል፤
- በክምችት፣ በማጓጓዝ፣ አጠቃቀም እና በአወጋገድ ወቅት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ቁጥጥር ያደርጋል፣ተገቢውን እርምጃም ይወስዳል፤
- ከፀረ-ተባይ እና መዳበሪያ አጠቃቀም ፣አከመቻቸት እና አወጋገድ ጋር በተያያዘ ከሰው ፣ ከእንስሳት እና የአከባቢ መመረዝ ስጋቶች አንፃር፣ ከኬሚካል ቅሪት ጋር በተያያዘ ደግሞ ከኤክስፖርት ኢኮኖሚ ወይም ከተመጋቢው ጤና አንፃር፣ ያሉ ስጋቶችን ለማስወገድ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሀገር-አቀፍስልጠና ይሰጣል፤
Plant Variety and Seed Regulatory Lead Executive
Veterinary Drugs Regulatory Lead Executive
- ለእንሰሳት መድኃኒት አምራች፣ አስመጪ እና ጅምላ አከፋፋይ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እና በተቋማት ውስጥ ለሚቀጠሩ ባለሙያዎች የሙያ ምዝገባና ፍቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፤
- የእንስሳት መድኃኒት፣ ክትባት እና የህክምና መሳሪያ ይመዘግባል፤ ያድሳል፤
- የእንሰሳት መድኃኒት አምራች፣ አስመጪ እና ጅምላ አከፋፋይ ተቋማትን በመመሪያው መሰረት ይቆጣጠራል፣ ግድፈት ሲኖር የማስተካከያ ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፤
- የእንሰሳት መድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ሲገባና ከአገር ሲወጣ ይቆጣጠራል፤
- አግባባዊ የሆነ የእንስሳት መድሃኒት አጠቃቀም እንዲሰፍን የሚያደርጉ ማንዋል፣ ጋይድላየን፣ ብሮሸር እና ፖስተር እያዘጋጃል፣ ያሰራጫል አስፈላጊም ሲሆን ስልጠና ይሰጣል፤
- የእንስሳት መድኃኒት፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና የተቋማት መረጃ ይሰበስባል፣ ያዘጋጃል፣ ለተጠቃሚ ተደራሽ ያደርጋል፤
- የእንስሳት መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት ይቀበላል፣ ጥናት ያካሂዳል ምላሽ ይስጣል፤
Animals Feed Regulatory Lead Executive
Head Center Coordination Office