የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ ሶስት መመሪያዎችን አፀደቀ።
**
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን (sticheting wageningen research ethiopia) ጋር በመተባበር የምግብ ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ ሶስት የተለያዩ መመሪያዎችን አፀደቀ።
ቢሾፋቱ መጋቢት 18 እና 19/2017ዓ.ም
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በመክፈቻ ንግግራቸው ባለስልጣኑ ከተቋቋመ 3 ዓመት ጀምሮ 64 የሚሆኑ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን 48 የሚሆኑትን በኦንላይን ዲታላይዜሽን እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው ባለስልጣኑ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች በዋነኛነት የምግብ ጥራት ደህንነትን ማረጋገጥ ሲሆን የተዘጋጁት መመሪያዎች ለቀጣይ ስራዎች ውጤታማነት ከፋተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።
የባለስልጣኑ የእፅዋት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው የፀደቁት መመሪያዎች በሰሊጥ ምርት ፣ በበርበሬ ምርት፣ የዶሮ ስጋና እንቁላል ምርት ላይ ሲሆን መመሪያዎቹ የምግብ ጥራት ደህንነትን ለማሻሻል ከፋተኛ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል።
የዘርፉ ባለሙያዎች በሶስቱ መመሪያዎች ላይ የሰሊጥ ምርት ጥሩ የሆነ አመራረት(good agricultural practices) እና የምርት አያያዝ ልምዶች (good heading practices)፣ የበርበሬ ምርት ጥሩ የሆነ የአመራረት ልምዶች (good agricultural practices) እንዲሁም የዶሮ ስጋና እንቁላል የደህንነት መመሪያ በተመለከተ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
ተሳታፊዎቹ በቀረቡት መመሪያዎች ላይ የተለያዩ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን አቅርበው እንዲካተቱ ተደርጓል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ የእንስሳት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል GAP እና GHP በመተግበር የሰሊጥ ምርትን እንዲሁም GAP፣ GHP እና GMPን የበርበሬ ምርትን ደህንነት ማሻሻል ፣የብክለት ስጋቶችን ለመቀነስና ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለአለም አቀፋ ገበያ ጥራትና ድህነቱን በማረጋገጥ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋል ያሉት ዶ/ር ሀሚድ በተለይም ተጠቃሚውን ህብረተሰብ ከምግብ ወለድ በሽታዎች ለመከላከል መመሪያዎቹ የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
********************//**********************
በሴቶች ተሳትፎ ሁለንተናዊ እድገት ይረጋገጣል!!!
*//***
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ 114ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ 49ኛ ጊዜ” ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል ተከበረ ።
አዳማ መጋቢት 5/2017ዓ.ም ኢ.ግ.ባ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በሴቶች ቀን ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ሴቶች በብዙ ትግሎች ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉና ትልቅ ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ባለስጣኑ በሚሰራው የቁጥጥር ስራ ላይ የተጠናከረና በአለም አቀፋ ደረጃ ተቀባይና እውቅና ያለው ተቋም ሆኖ እንዲሰራ የሴቶች ተሳትፎ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዕግስት ወንድማገኝ የሴቶችን ቀን ስናከብር ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊይና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ሲሆን በተለይ ሴቶች መብትና ግዴታቸውን በመጠቀም በማህበረሰቡ የሚደርስባቸውን ኋላቀር አስተሳሰብ በመታገል ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ አስተማሪና አረዕያ የሆኑ የታላላቅ ሴቶችን ተሞክሮም አቅርበዋል።
የባለሥልጣኑ የእንስሳት መድሀኒት ሪጉላቶሪ ምዝገባ ፈቃድ ዴስክ ኋላፊ ወ/ሪት ሰገዱ ሽፈራው በበኩላቸው በስራ ህይዎታቸው ያሳለፉትን ተሞክሮ ያቀረቡ ሲሆን አያይዘውም ከራሳቸው ተሞክሮ ተነስተው ሴቶች በተሰማሩበት ስራ ላይ የትኛውም ችግር ቢገጥማቸው የይቻላል መንፈስ በመያዝ ለቆሙለት ኣላማ በመታገል ውጤታማ እንዲሆኑ አስረድተዋል።
በመጨረሻም የባለሥልጣኑ የፅ/ቤት ኋላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው የቀረበው ተሞክሮ በጥንካሬ እንድንጓዝና መብትና ግዴታችን ተጠቅመን ውጤት እንድናመጣ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። ከዚህ ጋር አያይዘው የባለሥልጣኑ የስራ አመራር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አበበ ገለታ በበኩላቸው ሴቶች በሁሉም አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ የላቀ ነው በማለት እንደ ባለስልጣን መ/ቤት የሪጉላቶሪ ስራው ውጤታማ እንዲሆን ሴቶች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ገልፀው ለቀጣይ ስራችንም በጥንካሬና በቅንጅት ወደ ፊት መጓዝ እንዳለብን አሳስበዋል።
በብርቱካን አዲሱ
*****************//*******************************
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ኳራንቲን በ9 አገልግሎቶች ላይ ኦንላይን ሰርቪስ መጀመሩን አስታወቀ ።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በርካታ አገልግሎቶችን በኦንላይን ሰርቪስ እየሰጠ ይገኛል። ስለሆነም የእፅዋት ኳራንቲን በኦንላይን ሰርቪስ ባስጀመራቸው 9 አገልግሎቶች ላይ ከዘርፉ ባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
(የካቲት 25/2017ዓ.ም አዳማ ኢ.ግ.ባ)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ወደ አገር ውስጥ የሚገቡና ወደ ውጭ አገር የሚወጡ የግብርና ምርቶች፣ ግብዓትና ቴክኖሎጅ ጥራት፣ ደህንነትና ፈዋሽነት ላይ የቁጥጥር ስራ የሚሰራ ተቋም መሆኑን የገለፁት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዳለ ሀብታሙ በተለይም የቁጥጥር ስርዓቱ እንዲሳለጥና በአለምአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ተቋም እንዲሆን የኦንላይን ሰርቪስ አገልግሎት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ከፔራጎ የመጡት አቶ አቤል ተክላይ በበኩላቸው የኦንላይን ሰርቪስ አገልግሎት ሁሉም ተቋም መጠቀም እንዳለባቸውና በተለይም ሲስተሙ የአሰራር ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት እንዲኖር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
በመጨረሻም የእፅዋት ኳራንቲንና ሪጉላቶሪ የዕፅዋት ኢንስፔክሽን ሰርተፍኬሽን ዴስክ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ነጋ በተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ምላሽ በመስጠት በተለይም የኦንላይን ሰርቪስ አገልግሎት በተቋሙ ስታንዳርዱን የጠበቀና ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርዓት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
ፎቶ፦ በመንበረ ሀይሉ
**************************//****************************
የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች የዓድዋ ድል በዓልን አከበሩ
***//*****
የካቲት 20/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለ129ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓልን *ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል* በሚል መሪ ቃል የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አክብሯል፡፡
የዓድዋ ድል ገድል በመላው አለም የሚታወቅ የጥቁር ህዝቦች ድል የአሸናፊነት መገለጫ ሲሆን ልዩነታችን የምንለያይበት ሳይሆን አንድነትን የምንገነባበት ህብረ ቀለማችን አድርገን መውሰድ አለብን ሲሉ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር አክለውም አድዋን ስናስብ ጀግኖች አባቶቻችን በባዶ እግራቸው ተጉዘው የተደራጀ እና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ሳኖራቸው ያስመዘገቡትን ድል ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም በየተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ጠንክረን በመስራት ሌላ ድል በመፍጠር ለአሁኑና ለቀጣዩ ትውልድ መሰረት የሚሆን ስራ በመስራት የጀግኖች አባቶቻችንን ድል ማስቀጠል አለብን ብለዋል ፡፡
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስ እጅጉ፤ ዓድዋን እንዘክራለን፤ ኢትዮጵያን አፅንተን ለትውልድ እናሻግራለን! በሚል መሪ ሀሳብ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጽሁፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይትና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የባለስልጣኑ የዕጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወንዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የምታከብረው የአድዋ ድል በዓል የአሸናፊነት እና የሀያልነት የድል በዓል ነው ብለዋል፡፡
የማይደፈረውን የአባይ ግድብን በመገደብ ፤ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ከፍተኛ የሆነ የስንዴ ምርት በማምረት እና የተለያዩ ሀገርንና ህዝብን የሚጠቅም ሀገር ተሻጋሪ ሰራዎችን በመስራት የአሁኑ ትውልድም ድሉን ለማስቀጥል እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ወንዳለ ፤ ብሄር ፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ስራ በመስራት የሀገራችን ኢትዮጵያ የልማት ጉዞ እንዲፋጠን በቁርጠኝነት መስራት አለብን ብለዋል ፡፡
ዘጋቢ፡- መንበረ ሀይሉ
ፎቶ ግራፍ፡- ብርቱካን አዲሱ
****************************//**********************************
የብሔራዊ ዝርያ አፅዳቂ ቋሚ ኮሚቴ በቀረቡ ዕጩ ዝርያዎች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ!!
***
በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእፅዋት ዝርያና ዘር ጥራት ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚና ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በተገኙበት የብሔራዊ ዝርያ አፅዳቂ ቋሚ ኮሚቴ በእፅዋት ዘር ለቀቃ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ ።
የካቲት 19/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ
ጥራቱን የጠበቀ የተሻሻለ ዝርያ ዘር መጠቀም ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ የንግድ ስርዓቱ እንዲሳለጥ ክፍተኛ ሚና አለው ያሉት በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ ለዚህም የቀረቡ እጩ ዝርያዎችን የቀረበውን ዶክመንትና በመስክ በመገምገም በየጊዜው የመጨረሸ ውሳኔ በማሰጠት መረጃውን ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በተለይም የዝርያ አጽዳቂ ቋሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም በየአካባቢው የጸጥታ ችግር ሳይበግራቸው በመስክ የገመገሙ የቴክኒካል ኮሚቴ አባላትን ለስራው መቃናት ላደረጉት አስተዋጽዎ ሁሉ በራሳቸውና በባለሥልጣኑ ስም አመስግነዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢና የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕ/ር ፍሬው መክብብ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት አንዱ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎችን ብቃት በመረጃና በመስክ እንዲገመገሙ በማድረግ በብሔራዊ የዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ውሳኔ እንዲያገኙ እና ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው ተቀባይነት ያገኙ ዝርያዎችን ደግሞ በዝርያ መዝገብ እንዲካተቱ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ለቀጣይ ስራዎችም በተሻለ መልኩ በቅንጅት ከባለስልጣኑ ጋር እንደሚሰሩ አሳስበዋል።
በመቀጠል የውሳኔ ሰጪ ዳኞች/ የብሔራዊ ዝርያ ቋሚ ኮሚቴ አባላትና ከተለያዩ የፌደራልና የክልል የምርምር ተቋማት እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲና የግል ካምፓኒዎች የመጡ ሀላፊዎች በተገኙበት የዘርፉ ባለሙያዎች ከውጪ እና ከሀገር ውስጥ በቀረቡ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል።
በመጨረሻም ለውሳኔ ከቀረቡት 40 ዕጩ ዝርያዎች ውስጥ 28 ዝርያዎች ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን 12 ዝርያዎች ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ውድቅ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፏል።
ከተለቀቁ ዝርያዎች ውስጥ መካከል 3 Bt የበቆሎ ዝርያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፣ 1 Bt የጥጥ ዝርያ፣ 2 የኩችኔል ነፍሳት ጥቃትን የሚቋቋም የበለስ/ቁልቋል ዝርያዋች የሚገኙ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊና የዝርያ እና ዘር ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሀ ተሾመ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
****************************//*****************************
ባለስልጠኑ በሀገራዊ ጉዳዮች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቷል፡፡
*************//***************
( አዲስ አበባ የካቲት 18/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በሀገራዊ ጉዳዮች እና የመንግስት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት የካቲት 17/2017 ዓ/ም ውይይት አካሂደዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፤ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በግብርናው ዘርፍ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው ለዚህ ውጤት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የራሱን አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ተናግረዋል፡፡
የተቀመጡ የመንግስት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተጠናቅረውና ተደራጅተው ለውይይት መቅረባቸው ለቀጣይ ስራዎች ዉጤታማነት ወሳኝ በመሆናቸው እንደ ተቋም የተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን የዕቅዳችን አካል በማድረግ እና በመተግበር ጠንካራ የሆነ የግብርና ሬጉላቶሪ ተቋም በመገንባት የሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት እንድፋጠን ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መሰሉ ዋጋው ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ የመንግስት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ እንደ ተቋም የተመዘገቡ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች ፣ ሀገራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ተሳታፊዎች በስፋት ተወያይተዋል፡፡
የባለስልጣኑ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል፤ ከጥላቻና ማህበረሰብን ከሚጎዳ ትርክት በመውጣት ብሄራዊና ገዥ ትርክትን በሀገራችን በመገንባት እና በየጊዜው የሚነሱ የሰላምና ፀጥታ ችግሮች እንድፈቱ ከመንግስት እና ህዝብ ጎን በመሰለፍ በሀገራችን ሰላም እንድሰፍን ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል ፡፡
የባለስልጣኑ የዕጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንወዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው፤ ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት መፋጠን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ አመራሩና ሰራተኛው ራሱን በማብቃት በቅንነትና በታማኝነት ከብልሹ አሰራር የጸዳ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት በመስጠት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማነትን እንድረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ;- መንበረ ሀይሉ
ፎቶ ግራፍ ፡-ብርቱካን አዲሱ
*****************************//*****************************
በሀገር ደረጃ ተመሳሳይ የሆነ የዘር ጥራት ቁጥጥር ስረዐት እንድተገበር እየተሰራ ነው።
**
(የካቲት 15/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የክልል የዘር ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣናት እና ሌሎች ባለድርሻ እካላት በተገኙበት 13ኛውን አመታዊ የዘር ጥራት ቁጥጥር የጋራ የምክክር መድረክ ከጥር 13/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምዳሳደር ድሪባ ኩማ በምክክር መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የተሻሻለና ጥራቱ የተጠበቀ ዘር መጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ ከውጭ የሚገቡና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርጥ ዘሮች ጥራታቸው ተረጋግጦ ለተጠቃሚው እንዲደርስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ህገ-ወጥ የዘር ዝውውርን በመግታት፣ የህዝብን ጥቅም የሚያረጋግጥና መንግስት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ ወጥ የሆነ የዘር ጥራት ቁጥጥር ስረዓት እንዲኖር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከባለስልጣኑ ጋር በቅንጅትና በመደጋገፍ መስራት አለበት ብለዋል።
የባለስልጣኑ የዕጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ፤ የባለስልጣኑ የዘር ላብራቶሪ ማዕከል በአለም አቀፍ የዘር ጥራት ምርመራ ማህበር አባል መሆኑንና በቀጣይ አውቅና /Accrditation/ ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሀገር የሚገባ ማንኛውም የዘር አይነት በባለሥልጣኑ የዘር ላብራቶሪ ማዕከል እየተፈተሸ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአለም አቀፍ የዕጽዋት ጥበቃ ስምምነት መሰረት በሀገራት ደረጃ የዘር ዝውውር ሲደረግ በሽታና ሌሎች ባዕድ ነገሮች እንዳይገቡና እንዳይወጡ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች የተደነገገ መሆንኑን፣ በዘር አዋጅ ቁጥር 1288/2015 መሰረት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ውጭ የዘር ዝውውር እንደማይደረግ ገልፀዋል ፡፡
የምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭትን በተመለከተ ኦሮሚያ፣ አማራ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የተሻለ ሽፋን እንዳላቸው እና ሌሎቹም ክልሎች አፈፃፀማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእጽዋት ዝርያና ዘር ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ፍሰሀ ተሾመ፤ የዘር ጥራትን ለማረጋገጥ የምክክር መድረኩ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማጋራት፣ በቁጥጥር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመለየትና መፍትሔ የማስቀመጥ እንድሁም አብሮ የመስራት ባህል እንዲዳብር ከማድረግ አንጻር ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ፣ በክልል የዘር ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እና በባለ ድርሻ አካላት መካከል ወጥ የሆነ የዘር ጥራት ቁጥጥር እንዲኖር የጋራ ሰነድ በማዘጋጀትና በመፈራረም ዉይይቱ ተጠናቋል ::
ዘጋቢ:- መንበረ ሀይሉ
ፎቶግራፍ :-ብርቱካን አዲሱ
************************************//**************************
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዕፅዋት ጤንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትን ወደ ዲጅታል ቴክኖሎጅ ለመቀየር እየሰራ ነው፤
*
(አዲስ አበባ የካቲት 8 /2017 ዓ/ም ኢግባ)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የዕፅዋት ኳራንታይንና ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ ስር የሚሰጡትን የዕፅዋት እና የዕፅዋት ውጤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ዲጅታል ቴክኖሎጂ/ePhyto Solution/ ለመቀየር ለዕፅዋት ሬጉላቶሪ ዴስክ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት በኢሊሌ ሆቴል ስለጠና ተሰጥቷል፡፡
የዕፅዋት ኳራንታይንና ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት ተሰማ የስልጠናው ዋና አዓማ ከዚህ በፊት ሲሰጥ የነበረውን የዕፅዋት ጤንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና የጉምሩክ ማስለቀቂያ ሰርተፊኬት ከወረቀት ወደ ድጅታል ለመቀየር ነው ብለዋል ::
በ Brisk Solution Company Ltd አማካኝነት የበለጸገውን ePhyto Solution ሲስተም የዕፅዋት ሬጉላቶሪ ዴስክ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተግባር ስልጠና በመውሰድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚፈልገው መልኩ መሰራቱን ለማረጋገጥ ፣ የአለም አቀፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ መበልጸጉን ፣የበለጸገው ሲስተም ከIPPC-Hub ጋር Integrate መሆኑን ማረጋገጥ እና ክፍተቶች ካሉ የማሻሻያ ሀሳብና አስተያየት በመስጠት አገልግሎት አሰጣጡን በሚያመች መልኩ ለመገምገምና ወደ ተግባር ለማስገባት መሆኑን ገልፀው ስልጠናው ከTrade Mark አፍሪካ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አቶ ታምራት አክለውም የበለጸገው የ ePhyto Solution ሲስተም ተሻሽሎ አገልግሎቱን ለመስጠት ወደ ተግባር ሲገባ ለሁሉም የዕፅዋት ሬጉላቶሪ ባለሙያዎችና ለተመረጡ ለተቋሙ የዕጽዋት ዘርፍ ተገልጋዮች ስልጠና በመስጠት በሀገር ደረጃ ተሞክሮ በአለም አቀፍ ደረጃም አገልግሎቱ እንደሚተገበር ገልፀዋል፡፡
በኬንያ የሚገኘው ተጫራች Brisk Solution Company Ltd የePhytho የሲሰተም አናሊሰት ባለሙያ የሆኑት ሚስተር ሚካኤል ነዱአቲ የበለፀገውን ePhytho ሲስተም ለዕፅዋት ሬጉላቶሪ ዴስክ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ወደ ውጭ የሚላኩ እና ወደ አገር ውሰጥ የሚገቡ ከግብርና ምርቶች ጋር የሚገናኙ ሲስተሞችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ በሚገኘው የኔዘርላንድ ኢምባሲ የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፊኬሽን እስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሌክስ ሞሬት የተጫራቹ ድርጅት ያበለጸገው ePhyto Solution የአለም አቀፍ የዕፅዋት ጥበቃ ስምምነት/IPPC-Hub/ ስታንዳርድ ማሟላቱን፣ ከIPPC-Hub Integrate መሆኑን በሲስተም የተላከው ሰርተፊኬት የማረጋገጥ ስራ፣ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ እንዲኖር እንዲሁም መረጃዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የቅድመ ጥንቃቄዎች ስልጠና በመስጠት በዘርፉ ያላቸውን ልምድ በስልጠና ቆይታቸው አካፍለዋል፡፡
በመንበረ ሀይሉ
******************************//***************************
የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካትና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ለማሻሻል በሕግ ማዕቀፎች ላይ ግንዛቤ መፋጠር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በማዕከላዊ ማዕከል፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ማዕከሎች እንዲሁም ለጣቢያ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች በዕፅዋት ሪጉላቶሪ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የካቲት 07 እና 08/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ዝርያ ለቀቃና ዘር ጥራት ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋስሀ ተሾመ ስልጠናዉ ለአራተኛ ዙር መካሄዱን ገልፀው በተለይም የእፅዋት ሪጉላቶሪ የህግ ማዕቀፎችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በሚገባ ተረድተው በአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ላይ የሚታዩትን የአሰራር ክፍተቶች በማሻሻል ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በባለስልጣኑ የዕፅዋት ዘር ጥራት ሬጉላቶሪና የፀረ ተባይ ማዳበሪያ የዴስክ ሀላፊዎች በበኩላቸው የእፅዋት ሪጉላቶሪ የሕግ ማዕቀፎችን ፣የፀረ ተባይ እንስፔክሽን የፀረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር፣ የእፅዋት ዝርያ ዘር አዋጅ እና የማዳበሪያ ምዝገባ አዋጅና መመሪያ በተመለከተ እንዲሁም አጠቃላይ በባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባር ላይ በሕግ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስመረት ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል።
በመጨረሻም በቀረቡት አዋጅና መመሪያዎች ላይ ተሳታፊዎች ሰፊ ግንዛቤን እንደፈጠረላቸውና ውጤታማ ስራን ለመስራት እንደሚያግዛቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
*****************//******************************************
ኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በኢ-ሰርቪስ ኦን ላይን ላይ 36 አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ።
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሁሉም ስራዎች ላይ ወረቀት አልባ የሆነ ቴክኖሎጅን በመጠቀም እና የኢ- ሰርቪስ ኦንላይን አገልግሎቶችን በማበልፀግ ሰራተኞችን አስልጥኖ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ፡፡
ኢ.ግ.ባ የካቲት 7/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ዲሪባ ኩማ በመክፈቻ ንግግራቸው ባለስልጣኑ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣትና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የቁጥጥር ተቋም ለመፍጠር በተለይም ወረቀት አልባ የኢ-ሰርቪስ ኦንላይን ቴክኖሎጅን በመጠቀም ውስብስብ የአሰራር ሂደቶችን መቀነስና በተለይም ተገልጋዮች ከጊዜ፣ ከገንዘብና ሌሎች ጫና ከሚያደርስባቸው የአሰራር ሂደቶች ወጥተው ግልፅ፣ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎቶችን እንዲገኙ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣኑ መ/ቤቱ ሁሉንም አገልግሎቶች በኢ-ሰርቪስ ኦንላይን አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ሲሆን 38 የሚሆኑ አገልግሎትችን በኦንላይን ሰርቪስ እየሰጠ ሲሆን 27 የሚሆኑት በሂደት ላይ መሆናቸውን የገለፁት ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በፀደጉት አገልግሎቶች ላይ ባለሙያዎች በቂ ስልጠና አግኝተው ወደ ስራ መግባታቸውንም ተናግረዋል፡፡
ከፔራጎ የመጡት ባለሙያ አቶ አቤል ተክላይ የኢ ሰርቪስ ኦላይን አገልግሎት የአጠቃቀም ሂደቱንና ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ በዘርፉ ላሉ ባለሙያዎች አጭር ገለፃ አድርገዋል ።
በባለስልጣኑ የእንስሳት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው ሁሉም የአሰራር ስርዓቶች ዲታላይዜሽን ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ የአሰራር ስርዓታችንን ማዘመንና በቴክኖሎጂ የበለፀገ ተቋምን መገንባት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የዕፅዋት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የኢ-ሰርቪስ ኦንላይን ቴክኖሎጅ ተግባራዊይነት ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለመገንባት፣ ከተገልጋዮች ጋር ያለውን የአሰራር ስርዓት ግልፅና ቀልጣፋ ለማድረግና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት እንዲሁም ተቋሙ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
*******************************//*******************************
**** // *****
የተሻሻለው የዘር አዋጅ ለዘር ጥራት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ::
***
(አዳማ ጥር 30/2017ዓ.ም ኢግባ)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በተሻሻለው የዘር አዋጅ እና መመሪያዎች ላይ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአዳማ ከተማ አካሄደ።
በምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ግብርና
ባለስልጣን የእፅዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የተገኙ ሲሆን ፤ የዘር ጥራትን ለማረጋገጥ የተሻሻለው የዘር አዋጅ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የዘር ቴክኖሎጅ ትልቅ ድርሻ እንዳለው፤ አዋጁ ለዘር አስመጭዎች ለዘር አምራቾች እና አርሶ አደሮች ያለውን ፋይዳ በግልፅ ያስቀመጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ የዘርፉ ዋና ፈተና የሆነውን የሕገ-ወጥ ዘር ዝውውር ለመግታት ለውይይቱ ተሳታፊዎችን አደራ በመስጠት መድረኩን በበጀት ለደገፉ ለተቀናጀ የዘር ፕሪጀክት (ATI- ISSSEP) እና ለዘለቄታዊ ስርዓተ ምግብ ፕሮጀክት (FSRP) ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሻሻለውን የዘር እዋጅ ሰፊ ጊዜ በመውሰድ ያቀረቡት ዶ/ር ዳዊት ፀጋዬ፤ የተሻሻለው የዘር አዋጅ በአገልግሎት ሰጪው ተቋምና በአገልግሎት ፈላጊው መካከል ግልፅ የሆነ አሰራር እንዲፈጠር እንዲሁም ጥራት ያለው ዘር እንዲኖር እና የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት ይጠቅማል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የዝርያ ለቀቃ እና ዘር ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሀ ተሾመ፤ አዋጁም ሆነ ማስፈጸሚያ መመሪያዎቹ ሲዘጋጁ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መሆኑን ገልፀው የዘር አዋጁ ተሻሽሎ መዘጋጀቱ ጤንነቱ የተረጋገጠ ዘር በሀገሪቱ እንድኖርና ምርትና ምርታማነትን በመጠንና በጥራት ለማሳደግ ይጠቅማል ብለዋል::
ዘጋቢ:- መንበረ ሀይሉ
ፎቶግራፍ :-ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
*******************************************************
የዲጂታል አሰራር ስረዓት መዘርጋቱ ስራን በማቀላጠፍ ለብልሹ አሰራሮች በር ዘግቷል፤
******
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የፀረ- ተባይ እና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በየነ ንጋቱ (ዶ/ር)
(አዲስ አባባ -የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ጥር 13/2017)
የኢ-ሰርቪስ የኦንላይን አገልግሎት የስራ ክፍሉን የአገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን እና ከዚህ በፊት የሚነሱ ቅሬታዎችን በመቀነስ ፣ የአገልግሎት አሰራር ስረዓቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ በርካታ ዉጤቶች መገኘታቸውንና ለብልሹ አሰራርር የሚያጋልጡ አዝማሚያዎችንም ማስቀረት መቻሉን ዶ/ር በየነ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡
በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች በኦንላይን እንዲሆኑ አቅጣጫ ከማስቀመጥ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ጠቅሰው፤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ተግባር በመግባት በስራ ክፍሉ ያሉ አገልግሎቶችን ሙሉ በመሉ በኦንላይን እንዲሆኑ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል ።
ባለስልጣኑ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት ሰጭ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከተገልጋዮች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ሲባል ከዚህ በፊት አንድ ኬሚካል መዝግቦ ሰርተፊኬት ለመስጠት ከ 1አመትና በላይ የሚወስድ ሲሆን አሁን ግን በኦንላይን በመሆኑ አንድ ተገልጋይ ከ2 እስከ 3ወር አስመዝግቦ መጨረስ እንደሚችልና የአሰራር ስረዓቱ ቀልጣፋ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል፡፡
አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መሆናቸው ከመላው ኢትዮጵያ ክፍልና ከውጭ ሀገር አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች ወደ ተቋማችን ሲመጡ የሚደርስባቸውን እንግልትና አላስፈላጊ ወጭ በመቀነስ ቢሮ በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው፣ አገልግሎቶቹን በቤታቸው ወይም በስራ ቦታቸው ሆነው በእጅ ስልክ አማካኝነት፣ በተመቻቸው ጊዜና ሰዓት፣ በትንሽ ወጪ ቀልጣፋ አገልግሎት እንድያገኙ መደረጉን ገልጸዋል።
የፀረ- ተባይ እና ማዳበሪያ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከዚህ በፊት ከነበረው አድካሚ የአሰራር ስረዓት በመውጣት አሰራሩ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው በመሆኑ ማን፣ መቼ ፣ለማን ፣ ምን አይነት አገልግሎት እንደሰጠ በኦንላይን በግለጽ የሚያሳይ ሲሆን ስራዎችን በጊዜ ፣ በመጠንና በጥራት በውጤት ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል፡፡
አገልግሎቶች በኦንላይን መሰጠታቸው የስራ ክፍሉ ባለሙያዎች በተለያዩ ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ቢሮ መገኘት የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር የነበረውን የተገልጋዮች አገልግሎት መጓተት በመቀነስ ባሉበት ቦታ ሆነው በwi-fi በመታገዝ በእጅ ስልካቸው አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማድረግ ስራዎች እንዳይጓተቱ አግዟል ብለዋል፡፡
የስራ ክፍሉ አገልግሎቶች በኦንላይን እዲሆኑ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እና በመልካም ግንኙነት ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው፤ በዋናነት ክሮፕ ላይፍ ኢትዮጲያ አገልግሎቶች በኦንላይን እንዲሆኑ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ አገልግሎቱ እስከሚጀመር የተለያዩ ድጋፎችን እንዳደረገላቸው ገልጸዋል፡፡
ዲጅታላይዜሽን በዚህ ዘመን የዘርፈ ብዙ የለውጥ መሳሪያ በመሆኑ በስራ ክፍላችን ሲስተሙን በመጠቀም የምንሰጣቸውን ተግባራት ሙሉ በሙሉ በኦንላይን በማድረግ ስራዎቻችንን ግልጽ ፣ ቀልጣፋና ተገልጋይ ተኮር እንዲሆኑ በመስራት ለተገልጋዮቻችን እርካታን ፈጥረናል ፤ ባለስልጣኑ ተቆጣጣሪ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የአሰራር ስረዓቶችን በማዘመን ሌሎች ወደ ሲስተም ያልገቡ አገልግሎቶች በኦንላይን እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል በማለት ዶ/ር በየነ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234 በመንበረ ኃይሉ
**********
“አቅመ ደካሞችን በመርዳት ያለብንን ሰብዓዊ ሀላፊነት እንወጣ” (አቶ መሰሉ ዋጋው የፅ/ቤት ሀላፊ )
ጥር 20/2017ዓ.ም ኢ.ግ.ባ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ሥራ ስራ ክፍል በባለስልጣኑ የሚሰሩ የስራ ሀላፊዎችን በማስተባበር በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙ ህፃናትና አዋቂዎች የልብስ፣ የንፅህና መጠበቂያና የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ፡፡
የባለስልጣኑ ሴቶችና ማህበራዊ
ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትግስት ወ/አገኘሁ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ከሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ጋር በመሆን አቅመ ደካማ ለሆኑ አዋቂዎችና ህፃናት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተለይም በተለያዩ ምክንያቶች አካል ጉዳት የደረሰባቸውና ከፍተኛ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 2 ህፃናት በቋሚነት በተለያዩ ነገሮች ላይ ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው ገልፀዋል፡፡
የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሰሉ
ዋጋው በበኩላቸው አቅመ ደካሞችንና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ህፃናትን በመርዳት ያለብንን ሰብዓዊ ሀላፊነት እንወጣ ያሉ ሲሆን በተለይም ድጋፍ ላጡ ወገኖቻችንን መልካም ማድረግ አገራችንን መደገፍ ስለሆነ የጀምርነውን መልካም ስራ አጠናክረን መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል ።
(በብርቱካን አዲሱ)
*********
የሪጉላቶሪ ስርዓቱን ለማሳለጥ ኢንዲኬተር ጋይድ ላይን ወሳኝ መሆኑ ተገልፀ።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በተዘጋጀው ኢንዲኬተር ጋይድ ላይን ላይ ከቴክኒክ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አደረገ።
ጥር 23/2017 ዓ.ም
የተዘጋጀው ኢንዲኬተር ጋይድ ላይን አለምአቀፋዊ መሆኑ የሪጉላቶሪ ስርአቱን ያሳልጠዋል ያሉት የባለስልጣኑ የእንስሳት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም /ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በተለይም እቅዱ የታሰበውን አላማ እንዲያሳካ የሚቀርቡት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ወሳኝ መሆናቸን ገልፀዋል።
የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሰረት አበባው በእፅዋት ሪጉላቶሪ ፣ በእንስሳት ሪጉላቶሪ እና ሜካናይዜሽን ላይ እንዲሁም ሌሎች ስራዎች ላይ ያሉትን ኢንዲኬተሮች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ላይ በቴክኒክ ባለሙያዎች ሰፊ ግብዓቶች ተወስደው ለቀጣይ ዕቅዱ ተስተካክሎ የሚቀርብ ይሆናል ብለዋል ።
ዘጋቢ-: ብርቱካን አዲሱ
*****
የዕፅዋትና ዘር ጥራትና ጤንንት ለማስጠበቅ የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡
****
(ጥር 26/2017 ዓ/ም ኢ.ግ.ባ አዳማ)
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የዕፅዋት ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ የጤና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት/ Phytosanitory certificate እና ተያየዥ አሰራሮች ዙሪያ በተመለከተ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የዕፅዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ፤ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አጠቃላይ ወደ ውጭ በሚላኩና ወደ ሀገር ውሰጥ በሚገቡ እጽዋት፣ የእጽዋት ውጤት እና ዘርን በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያን የሚወክል ብቸኛ የግብርና ምርት ጥራት ተቆጣጣሪ ተቋም/Bio security Authority/ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ወንወዳለ አክለውም ወደ ሀገር የሚገቡ ዕፅዋት፣ የዕፅዋት ውጤት እና ዘርን ጨምሮ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የዕፅዋት በሽታ ፣ ተባይ እና ጎጅ አረሞች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ ፤ በዚህ ምክንያት ሀገራችን ውስጥ ያሉ ዘሮችንና ምርቶችን ከጥቅም ውጭ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ስለሆነም ይህንን ሀገር ሊያጠፋ የሚችል ምንጩ ያልታወቀ እና ያልተመረመረ እጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ምርቶች እንዳይገቡ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን ጥራቱና ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እና የዕፅዋት ጤንነት የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሌለው ሀገርን ሊጎዳ የሚችል ዘር እና የእጽዋት ምርት እንዳይገባ ተገቢውን ፍተሻ፣ ክትትልና ጥቆማ በማድረግ ለሀገራችሁ ታማኝ ሆናችሁ እንደ ሀገር ጠባቂ ወታደር በታማኝነትና በቁርጠኝ በትብብር መስራት አለባችሁ በማለት አቶ ወንዳለ አሳስበዋል፡፡
የባለስልጣኑ የዕፅዋት ጤና አማካሪ የሆኑት አቶ ፍቅሬ ማርቆስ በዕፅዋት ጤናና ዘር ሬጉላቶሪ ተግባራት አፈጻጸም የግንዛቤ ማሳደጊያ አውደ ጥናት ላይ የመወያያ መነሻ ጽሁፍ ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ የግንዛቤ ማስጨበጫው ዋና አላማ ቀልጣፋና ውጤታማ የዕፅዋት ኳራንታይንና ዘር ቁጥጥር ተግባራትን ለማከናወን የጋራ ዓላማ ከሚጋሩ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት እየጨመረ የመጣውን የባዕድ ጎጅ ተባዮች ስጋት በመቀነስ ባእድ ጎጅ ተባዮች በቀላሉ ወደ ሀገር እንዳይገቡ፣ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች በተባይ ጉዳት ምክንያት ከገበያ ውጪ እንዳይሆኑ፣ አገልግሎቱን በብቃት ለመስጠት እና የባለስልጣኑን ተልዕኮ ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ከግምሩክ ኮሚሽን ፣ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ፣ከኢትዮጵያ አየር መንገድ(ካርጎ) ፣ ከእጽዋትና ዘር አስመጭና ላኪ ድርጅቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን፤ የቀረበውን የመወያያ ሰነድ እና በስራ ላይ ያጋጠሟቸውን ችግሮች መነሻ በማድረግ የተለያዩ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አንስተው የጋራ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሶ ለቀጣይ ስራም በጋራና በትብብር ለመስራት ቃል ገብተዋል ፡፡
በመጨረሻም የመወያያ ጽሁፉን ያቀረቡት አቶ ፍቅሬ ማርቆስ፣ የዕፅዋት ኳራንታይን እና ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት ተሰማ እና ሌሎች ከባለስልጣኑ የተሳተፉ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችና ስራ አስፈጻሚዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተው፤ የእጽዋት ጤንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያልያዙ ዘሮችና ዕፅዋቶች በተለያዬ መንግድ ማለትም በመንገደኞች አማካኝትና በፖስታ ቤት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን በቅንጅትና በትብብር ልንሰራ ይገባል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በመንበረ ሀይሉ
*****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የ2017 የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
***
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የ2017 የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ላይ የባለስልጣኑ በየዘርፉ ያሉ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ግምገማ አካሂዷል፡፡
(ጥር 13 /2017 ዓ.ም ) ኢ.ግ.ባ
በግምገማ መድረኩ ላይ ንግገር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ፤ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልእኮ በብቃት ለመወጣት ስትራቴጅክ እቅድ በማቀድ ያለውን ሀብት፣ የሰው ሀይል፣ ለውጥ እና የተገኝ ውጤት አስተሳስሮ በመምራት ተቋሙን ወደ ተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ጨምረውም ባለስልጣኑ ውጤታማ የሆነ የአሰራር ስረዓት በመዘረጋት፣ የሰራተኞችን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎች የማመቻቸት ስራዎች፣ የተለያዩ የህግ ማእቀፎችን የማዘጋጀት ስራዎች፣ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን የመለየትና የመፍታት ብቃትን በማሳደግ፣ ጠንካራ የሆነ የስራ ባህል በማዳበር ፣አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት እና ቅንጂታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በአለም አቀፍ ደረጃ በግብርናው ዘርፍ ተወዳዳሪ የሆነ የሬጉላቶሪ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈ ተቋሙ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከመስጠት ባለፈ የቁጥጥር ስራውን በመመርመር እና አለም አቀፍ የሬጉላቶሪ ተቋም ህጎችን ጠብቆ እና አክብሮ በመስራት የሚሰሩ ስራዎች ጥራትና ደህንነታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
የባለስልጣኑ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሰረት አበባው የ6 ወር እቅድ አፈጻጻም ሪፖርት ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤በ6ወሩ የተመዘገበው ውጤት ለቀጣይ ስራዎች ውጤታማነት ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በግምገማው ተሳታፊ የነበሩ የስራ ሀላፊዎች በ6ወሩ የተመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም ለቀጣይ ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸው፤ ስራዎችን በውጤት ለመስራት ያልተሟሉ ግብዓቶች፣ የሰው ሀይል እጥረት እንድሁም ስራዎችን ለመስራት እንቅፋት የሆኑ ችግሮች በአጭር ጊዜ እንድፈቱ በማለት አስተያየታቸውን አንስተዋል፡፡
የባለስልጣኑ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው የተቋሙ የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸው፤ በአንጻሩ ደግሞ በኢንስፔክሽን ስራዎች ላይ የአፈጻጸም ውስንነት መታየቱን ጠቁመው፤ስራዎችን ለመስራት ያልተሟሉ ግብዓቶች በአጭር ጊዜ እንድሟሉ እንድሁም የታዩ የአፈጻጸም ውስንነቶችን በመገምገም ወደ ስራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የባለስልጣኑ የእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የአሰራር ስረዓቱን ለማዘመንና ውጤታማ ስራ ለመስራት ሁሉም የተቋሙ አገልግሎቶች በኢ-ሰርቪስ እንድሆኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመነጋገር እየተሰራ መሆኑኑን፤ እንድሁም የአሰራር ሂደቱን በመጠበቅ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የማበረታቻ ስረዓት በመዘርጋት እውቅና እንደሚሰጥና የአፈጻጸም ችግር ላለባቸው ደግሞ ከችግራቸው እንድወጡ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
በመንበረ ኃይሉ
*********
የዲጂታል አሰራር ስረዓት መዘርጋቱ ስራን በማቀላጠፍ ለብልሹ አሰራሮች በር ዘግቷል፤
******
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የፀረ- ተባይ እና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በየነ ንጋቱ (ዶ/ር)
(አዲስ አባባ -የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ጥር 13/2017)
የኢ-ሰርቪስ የኦንላይን አገልግሎት የስራ ክፍሉን የአገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን እና ከዚህ በፊት የሚነሱ ቅሬታዎችን በመቀነስ ፣ የአገልግሎት አሰራር ስረዓቱን ቀልጣፋና ግልጽ የሆነ በማድረግ በርካታ ዉጤቶች መገኘታቸውንና ለብልሹ አሰራርር የሚያጋልጡ አዝማሚያዎችንም ማስቀረት መቻሉን ዶ/ር በየነ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡
የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች በኦንላይን እንዲሆኑ አቅጣጫ ከማስቀመጥ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ጠቅሰው፤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ተግባር በመግባት በስራ ክፍሉ ያሉ አገልግሎቶችን ሙሉ በመሉ በኦንላይን እንዲሆኑ በማድረግ የተገልጋዩን ያልተገባ እንግልት ፣ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት በመቆጠብ ግልጽና እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደተቻለ ተናግረዋል ።
ባለስልጣኑ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት ሰጭ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከተገልጋዮች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ሲባል ከዚህ በፊት አንድ ኬሚካል መዝግቦ ሰርተፊኬት ለመስጠት ከ 1አመትና በላይ የሚወስድ ሲሆን አሁን ግን በኦንላይን በመሆኑ አንድ ተገልጋይ ከ2 እስከ 3ወር አስመዝግቦ መጨረስ እንደሚችልና የአሰራር ስረዓቱ ቀልጣፋ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል፡፡
አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መሆናቸው ከመላው ኢትዮጵያ ክፍልና ከውጭ ሀገር አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች ወደ ተቋማችን ሲመጡ የሚደርስባቸውን እንግልትና አላስፈላጊ ወጭ በመቀነስ ቢሮ በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው፣ አገልግሎቶቹን በቤታቸው ወይም በስራ ቦታቸው ሆነው በእጅ ስልክ አማካኝነት፣ በተመቻቸው ጊዜና ሰዓት፣ በትንሽ ወጪ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል።
የፀረ- ተባይ እና ማዳበሪያ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከዚህ በፊት ከነበረው አድካሚ የአሰራር ስረዓት በመውጣት አሰራሩ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው በመሆኑ ማን፣ መቸ ፣ለማን ፣ ምን አይነት አገልግሎት እንደሰጠ በኦንላይን በግለጽ የሚያሳይ ሲሆን ስራዎችን በጊዜ ፣ በመጠንና በጥራት በውጤት ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል፡፡
አገልግሎቶች በኦንላይን መሰጠታቸው የስራ ክፍሉ ባለሙያዎች በተለያዩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቢሮ መገኘት የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር የነበረውን የተገልጋዮች አገልግሎት መጓተት በመቀነስ ባሉበት ቦታ ሆነው በwi-fi በመታገዝ በእጅ ስልካቸው አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማድረግ ስራዎች እንዳይጓተቱ አግዟል ብለዋል፡፡
የስራ ክፍሉ አገልግሎቶች በኦንላይን እዲሆኑ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እና በመልካም ግንኙነት ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው፤ በዋናነት ክሮፕ ላይፍ ኢትዮጲያ አገልግሎቶች በኦን ላይ እንዲሆኑ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ አገልግሎቱ እስከሚጀመር የተለያዩ ድጋፎችን እንዳደረገላቸው ገልጸዋል፡፡
ዲጅታላይዜሽን በዚህ ዘመን የዘርፈ ብዙ የለውጥ መሳሪያ በመሆኑ በስራ ክፍላችን ሲስተሙን በመጠቀም የምንሰጣቸውን ተግባራት ሙሉ በሙሉ በኦንላይን በማድረግ ስራዎቻችንን ግልጽ ፣ ቀልጣፋና ተገልጋይ ተኮር እንዲሆኑ በመስራት ለተገልጋዮቻችን እርካታን ፈጥረናል ፤ ባለስልጣኑ ተቆጣጣሪ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የአሰራር ስረዓቶችን በማዘመን ሌሎች ወደ ሲስተም ያልገቡ አገልግሎቶች በኦንላይን እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል በማለት ዶ/ር በየነ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
በመንበረ ኃይሉ
**********
በማእከላዊ ማእከል ስር ለሚገኙ የጣቢያ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች በእፅዋት ሬጉላቶሪ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
*
ታህሳስ 26 እና 27/2017 ዓ/ም አዳማ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን
የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካትና የአገለግሎት አሰጣጥን ስርዓትን ለማሻሻል በአፈጻፀም የሚስተዋሉ ችግሮችን እና ክፍተቶችን በመቅረፍ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የተላበሰ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በዚህ ረገድ የማእከላዊ ማእከል የሚገኙ ጣባያዎች አብዛኛው የወጪ ገቢ ንግድ እቃዎች ዝውውር የሚካሄደበት በመሆኑ እና ከባለጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላው እንዲሁም ከባለጉዳይ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ቀጥተኛ በመሆኑ በነዚህ ጣቢያዎች የሚሰሩ ባለሞያዎች እና ሃላፊዎች ያሉትን የህግ ማዕቀፎች በጥልቀት ሊረዱዋቸው ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት ይህንን ታሳቢ ያደረገ ስልጠና ከአለም የምግብና እርሻ ድርጅት ጋር በመተባበር ከ ታህሳሳ 26-27 2017 ዓ/ም በአዳማ ከተማ ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የከፈቱት የፀረ ተባይ እና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ በየነ ንጋቱ (ዶ/ር) ስልጠናው ለሶስተኛ ዙር መካሄዱን እና በአንደኛ እና በሁለተኛ ዙር በባለስልጣኑ የሚገኙ የእፀዋት ዘርፍ ባለሞያዎች ተሳታፊ እንደበሩ ገልፀው በዚህ በሶስተኛው ዙር በማእከላዊ ማእከል ኢትዮጵያ የሚገኙ ጣቢያዎች ወጪ ገቢ ምርቶችን የሚበዙበት በመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን የአሰራር ክፍተት ለመቅረፍ በመስኩ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ አያይዘው ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ የህግ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስመረት ጠቅላላ የባለስልጣኑን ስልጣንና ተግባር በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ በተዋረድ ያሉ ቴክኒካል ባለሞያዎች (እንስፔክተሮችን ስልጣን ፣ሃላፊነት እና ተጠያቂነት ላይ ማብራራያ ሰጥተዋል፡፡
በመቀጠልም ከእፅዋት ኳራንታይን አቶ ፍቅሬ ማርቆስ በእፅዋት ኳራንታይን ሬጉላቶሪ ያሉ የሕግ ማዕቀፎችን ከመጀመሪዎቹ ጀምሮ አሁን በስራ ላይ እስካሉት ድርስ በዝርዝር አቅረበዋል፡፡
የባለስልጣኑ የፀረ ተባይ ምዝግባና ቁጥጥር ዴስክ ሀላፊ አቶ ብርሀኑ የፀረ-ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ፣ አቶ መኩሪያው ዋለ የእፅዋት ዝርያ ዘር በተመለከተ እንዲሁም የማዳበሪያ ምዝገባ ቁጥጥር ዴስክ ሀላፊ ግርማ ንጉሴ በማዳበሪያ ምዝገባ አዋጅና መመሪያ ላይ ሰፊ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ላይ በተሳታፊዎች ግልፅ ውይይት ተካሂዷል።
በመጨረሻም በተሳታፊዎች በተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ በሚመለከታቸውሀላፊዎችና ባለሙያዎች ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን በባለስልጣኑ ማዕከላዊ ማዕከላት ፅ/ት ሀላፊ ዶ/ር ገመዳ ቢነግዴ የመዝጊያ ንግግር አድርገው ስልጠናው ተጠናቋል።
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
****
በማዕከላዊ ማዕከል ስር ባሉ ስድስት ጣቢያዎች የታዩ የአሰራር ክፍተቶች ላይ ውይይት ተካሄደ
**
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የቴክኒክ ሀላፊዎች፣ የማዕከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የማዕከላዊ ማዕከል ሀላፊ እንዲሁም የጣቢያ ሀላፊዎችና ሙያተኞች በተገኙበት የአሰራር ክፍተቶች ላይ ውይይት ተካሄደ።
(ታህሳስ 25 ቀን 2017ዓ.ም አዳማ )
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በግብርናው ዘርፍ ያለውን የሪጉላቶሪ ስርዓት ውጤታማ ለማድረግና የተሻለ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ ያስችላል ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በተለይም በየስራ ክፍሉ የሚታዩትን የአሰራር ክፍተቶች በመለየትና ውስን የሆነውን የህዝብን ሀብት ከብክነት በመጠበቅ እንዲሁም ከሙስና የፀዳ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዚህም መሰረት በማዕከላዊ ማዕከል ስር ባሉ ስድስት ጣቢያዎች ላይ የታዩ የአሰራር ክፋተቶች ተለይተው ለውይይት የቀረቡ ሲሆን የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ለቀጣይ ስራቸው በግብዓት ወስደው ለችግሮቹ መፋትሄ እንደሚያስቀምጡ ተናግረዋል ።
የባለሥልጣኑ የእፅዋት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው በአብዛኛው የታዪት የአሰራር ክፍተቶች የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት አለመኖር ነው በማለት ለቀጣይ ስራዎች በተናበበና በተቀናጀ ሆኔታ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ በተቋቋመበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳካቸውን ስራዎች ግብ ለማድረስ የክትትልና የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የእንስሳት ዘርፍ ሬጉላቶሬ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በአሰራር ስርዓቱ ላይ የህግ ማዕቀፍ ችግሮች፣ የአቅም ክፍተትና በቅንጅት አለመስራት የታዩ ሲሆን እነዚህን ችግሮች በመፍታት ማህበረሰብንና አገርን ማገልገል ይገባል ሲሉ ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ አሳስበዋል።
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
****
የላብራቶሪ ደህንነትና ጤና አጠባበቅ ላይ የሰራተኞችን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል፤
***
(ሰበታ ታህሳስ 25/2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን)
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራት ምርመራ ማዕከል ባለሙያዎች በላብራቶሪ ደህንነትና ጤና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከታህሳስ 24/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ተሰጥቷል፡፡
የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራት ምርመራ ማዕከል የላብራቶሪ ጥራት ማኔጅመንት ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዘርይሁን አበጋዝ፤ የስልጠናው ዋና አላማ የላብራቶሪ ማዕከሉን ነባር፣ አዲስና በዝውውር ማዕከሉን የተቀላቀሉ ሰራተኞች የላብራቶሪ ደህንነትና ጤና አጠባበቅ በተመለከተ የኬሚካሎችን ፣የተህዋሲያንን እና የላብራቶሪ መሳሪያዎችን አይነት ፣ባህሪ ፣አያያዝ ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ እንድሁም በስራ ላይ እያሉ አደገኛ ኬሚካሎችና ተህዋሲያን ከአጠቃቀምና ጥንቃቄ ጉድለት ሊያስከትሉ የሚችሉትን ችግሮች በመረዳት የራሳቸውን ጤንነት፣ የአካባቢያቸውንና የስራ መሳሪያዎችን ደህንነት እንድጠብቁ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡
በስልጠና መድረኩ ላይ የላብራቶሪ ደህንነትና ጤና አጠባበቅን በተመለከተ በዘረፉ ባለሙያዎች የተለያዩ የስልጠና ርእሶች ለተሳታፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የባለስልጣኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትዕግስት ወ/አገኘሁ በበኩላቸው ሰልጠናው ባለሙያዎች በስራ ላይ እያሉ የሚያጋጥሟቸውን የጤና እና የተለያዩ ችግሮች የሚቀንስ እና በዋናነት ደግሞ ሴት ሰራተኞች ለአደጋ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የሚረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ የሴት ሰራተኞች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ እና የስራ አካባቢ ደህንነትን ከመጠበቅ አንጻር ከላብራቶሪ ማዕከሉ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ወ/ሮ ትዕግስት ወ/አገኘሁ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው ከስራችን ባህሪ አንጻር አስፈላጊና የኬሚካሎችን፣ የተህዋሲያንና የላብራቶሪ መሳሪያዎችን ባህሪ፣ አያያዝና አጠቃቀም እንድሁም ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት በመረዳት ራሳችንንና የስራ አካባቢያችንን ደህንነት እንድንጠብቅ ይረዳናል ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
ከስልጠናው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ምላሽ በመስጠት በላብራቶሪ ማዕከሉ ያሉ ሁሉም ሰራተኞች የሚሰጠውን ሰልጠና በአግባቡ እና በጥንቃቄ ስራ ላይ በማዋል የራሳቸውን ፣ የስራ ባልደረባቸውን እና የአካባቢያቸውን ደህንነት በመጠበቅ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ዶ/ር ዘርይሁን አበጋዝ ሰልጣኞችን አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
በመንበረ ኃይሉ
****
የግብርና ሜካናይዜሽን ረቂቅ መመሪያዎች ማበልጸጊያ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ ።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ሜካናይዜሽን ረቂቅ መመሪያዎች ማበልጸጊያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ ። (ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም) አዳማ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በመክፈቻ ንግግራቸው የረቂቅ መመሪያው ተፈፃሚነት በዋነኝነት ግልጽና ተደራሽ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት አገልግሎት ሰጪዎች የሚመዘገቡበት የአገልግሎታቸውም ብቃት ተመዝኖ እውቅና የሚያገኙበት ስርዓት በመፍጠር ወቅታዊ የማስተካከያ እርምጃዎችን እና ቀጣይ የማሻሻያ ስራዎችን ለማከናወን እንዲሁም አገልግሎት ሰጪዎች አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟላ የግብርና መሳሪያ ባለሙያ መጠቀማቸውን በመከታተልና በማረጋገጥ ጥራት ያለዉ አገልግሎት ለተጠቃሚው እንዲሰጥ ማድረግ ነው ብለዋል።
የግብርና ምርምር ኤክስቴንሽንና ሜካናይዜሽን ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን አመዴ በበኩላቸው የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር …../2017 ላይ እና የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች አምራች አስመጪና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር ረቂቅ መመሪያ ቁጥር …./2017 በተመለከተ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
የባለሥልጣኑ የእንስሳት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ገልፀው የግብርና ዘርፉን ለማዘመን የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም አካል በትኩረትና በሀላፊነት መስራት እንዳለበት ገልፀው መመሪያውን ማፅደቅ በተመለከተ በትኩርትና በሀላፊነት እየተሰራበት ስለሆነ በአጪር ጊዜ ውስጥ ፀድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የባለስልጣኑ የእፅዋት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የሜካናይዜሽን ረቂቅ መመሪያ የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግና ለማዘመን እንዲሁም የንግድ ስርዓቱን ለማሳለጥ ያግዛል ብለዋል።
በአጠቃላይ የቀረበው ረቂቅ መመሪያ የሪጉላቶሪ ስርዓቱን ወደ ተሻለ የአሰራር ስርዓት ለማምጣት ያስችላል ያሉት ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በተሳታፊዎች በተነሱት ሀሳብና አስተያየቶች ላይ ምላሽ ሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል።
ዘጋቢ ፦ ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
****
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ዝርያና ዘር ሪጉላቶሪ ከአፋርና ሱማሌ ክልል የግብርና ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ፤
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) ጋር በመተባበር ከአፋርና ሱማሌ ክልል ለተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች በዘር ጥራት ቁጥጥር ስራና ለሰራው የሚያስፈልጉ መሰረታዊ አደረጃጀት፣ ሎጀስቲክ፣ በመሳሰሉት ላይ ከሌሎች ክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በመቀናጀት ልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡
በልምድ ልውውጡ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የዕጽዋት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ ጥራቱ የተመሰከረለት ምርጥ ዘር አቅርቦት፣ የሬጉላቶሪ ተቋማት ሚና እና የአፋርና ሶማሌ ክልሎች ካላቸው የተፈጥሮ ጸጋ አኳያ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እንደሆኑ በመጥቀስ በሌላ በኩል ከጎረቤት ሀገር ጋር በድንበር አዋሳኝ ክልሎች ስለሆኑ ለህገ-ወጥ ንግድ የተጋለጡ ስለሆኑ የአሰራር ስርዓቱን ማዘመን እንደሚገባ በማንሳት የአለም አቀፍ የሬጉላቶሪ ልምዶችን በተመለከተ አጠቃላይ ምን እንደሚመስሉ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከCatholic Relief Services, CRS አቶ አጋዤ በበኩላቸው የፕሮጀክቱን አላማ፣ የሚደግፋቸውን ክልሎች፣ በተለይም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰብሎች ላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውና እንዲሁም ከልምድ ልውውጡ ምን ይጠበቃል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ስፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የባለስልጣኑ የእጽዋት ዝርያና ዘር ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሀ ተሾመ የመስሪያቤቱን አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም በዘር ጥራት ቁጥጥር ዙሪያ እተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ ከክልሎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘው ፕሮጀክቱ ከሚያቅፋቸው ስድስት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ) የተወጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎቹ የየክልላቸውን ልምድ በስፋት በማቅረብ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
ባለሙያዎቹ በልምድ ልውውጡ ላይ ጥሩ ልምዶችን እንዳገኙና ባገኙት ልምድ ተነስተው ወደ ስራ እንደሚገቡ አሳስበው በተለይ ደግሞ ውጤታማ ስራ ለመስራት የቁጥጥር ማእከላትን ማቋቋምና በየደረጃው ላሉ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ የግብርና ባለስልጣን ላብራቶሪን እና የኦሮሚያ ግብርና ግብዓቶችና ምርት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና መስሪያቤት እንዲሁም በስሩ በሚገኙ የጥራት ቁጥጥር ማዕከላት ውስጥ የአሰላ ቅርንጫፍን እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
ዘጋቢ፡- ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ: Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡ eaapr_1234
————– ——————- ———–
የስራ አፈፃፀም እቅድ እና ምዘና ስረዓት ውጤታማ እንድሆን የሰራተኛውን አቅም ማሳደግ ይገባል ፤
****
( አዳማ ታህሳስ 18 2017 ዓ /ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን )
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በስራ አፈፃፀም እቅድና ምዘና ላይ ለተቋሙ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ ::
በመድርኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስለጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የስልጠናው ዋና አላማ አንደ ተቋም በስራ አፈፃፀም እቅድና ምዘና ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችንና ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና በቀጣይ በግልፅነት ፣ በተጠያቂነትና በመተማመን ላይ የተመሰረተ የምዘና ስረዓት እንድኖር ለማስቻል ነው ብለዋል ::
የተቋሙን ተልእኮ ለማሳካትና የመፈፀም አቅም ለማጎልበት ሕጋዊ ማእቀፍን ማሻሻል ፣ ድጅታል አሰራርን መዘርጋት እንድሁም የባለሙያውን አቅም የመገንባት ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ::
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ተቋሙ የሬጉላቶሪ ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን ይህንንም ውጤታማ ለማድረግ ከቅሬታና ብልሹ አሰራር የፀዳ ስራ በመስራት ራሳችሁን አንደ ሀገር ጠባቂ ወታደር በማሰብ በምናደርጋቸው የቁጥጥር ስራዎች ላይ ጥራትና ደህንነትን በማስጠበቅ ህዝብንና ሀገርን ለመጥቀም የተሰጣችሁን ተግባርና ሀላፊነት በብቃትና በታማኝነት መፈፀም አለባችሁ ሲሉ ሰልጣኞችን አሳስበዋል ::
በሌላ በኩል የስራ አፈፃፀም እቅድና ምዘና በተመለከተ በብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ በአቶ ቦጋለ በቀለ ፣ የስራ አፈፃፀም እቅድ ዝግጅትና ምዘና በብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ በወ/ሪት ብርቱካን ቦጋለ እና የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታትን በተመለከተ በተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈፃሚ በአቶ አበበ ለማ የስልጠና መነሻ ፅሁፎች ለሠራተኞች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል ::
ስልጠናው በስራ አፈፃፀም እቅድና ምዘና ላይ ያላችውን ግንዛቤ የሚጨምርና ከዚህ በፊት የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ግልፅና ስራን መስረት ያደረገ የአፈፃፀም ምዘና እንድደረግ ያግዛል ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናግረዋል ::
የባለሥልጣኑ ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገለታ በበኩላችው ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ስልጠናው በሰራተኛው እና በአመራሩ መካከል ቅሬታን በመቀነስ መተማመንና ግልፀኝነት እንድፈጠር ያደርጋል በማለት ገልፀዋል ::
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
በመንበረ ኃይሉ
የሬጉላቶሪ ሥርአቱን ለማዘመን የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ወሳኝ ነው :: ****
( አዲስ አበባ ታህሳስ 8 2017 ዓ /ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን )
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መድሃኒት ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈፃሚ በተመረጡ አገልግሎቶች ላይ የኦላይን አገልግሎት ለመስጠት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ ::
በእንሰሳት መድሃኒት ሬጉላቶሪ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአት ለማዘመንና ለማሳደግ በርካታ ተግባራት እየተክናወኑ ይገኛሉ ::
እነዚህንም ተግባራት ጥራታችውን ጠብቀው ውጤታማ በሆነ መልኩ እንድፈፀሙ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ትኩረት የሚሰጠው እና አስፈላጊ ጉዳይ ነው ::
የእንስሳት መድሃኒትና ተቋማት ምዝገባና ፈቃድ ደስክ ኃላፊ ወ /ሮ ሰገዱ ሽፈራው ከዚህ በፊት የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ስረዓት ለማዘመንና ቀልጣፍ ለማድረግ በዘርፉ በተመረጡ ተግባራትን በኢ-ሰርቪስ የኦላይን አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው በዛሬው እለት ደግሞ በአዲስና ነባር የተቋማት ምዝገባና ፈቃድ እንዲሁም አዲስና ነባር የባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ምዝገባና አድሳት ላይ የሚሰጠውን አገልግሎት የዘርፉ ባለሙያዎች ሲስተሙን ተጠቅመው ተገልጋዮች የሚፈልጉትን አገልግሎት በኦላይን እንድያገኙ ለማድርግ የሚያስችል ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ገልፀዋል ::
በሌላ በኩል ስልጠናውን እየከታተሉ ያሉ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው የኢ-ሰርቪስ የኦላይን አገልግሎት ስልጠና ለስራችን አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል ::
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
በመንበረ ኃይሉ
——————————-
የኢ-ሰርቪስ የኦንላይን አገልግሎት ጊዜን በመቆጠብ ስራን ያቀላል- ዶ/ር ሀሚድ ጀማል
**
(አዲስ አባባ፣ ታኅሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን)
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በእንስሳት መድኃኒት ሬጉላቶሪ ዘርፍ በተመረጡ 5/አምስት/ አገልግሎቶች ላይ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት በኦንላይን ለመስጠት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለእንስሳት መድሃኒት አስመጭና ጅምላ አካፋፈዮች ስልጠና ሰጠ፡፡
በመርሃ ግበሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በእንስሳት ሀብት የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዝ ሲሆን ለዚህም ጥራቱ ፣ደህንነቱ እና ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት መድሃኒት አቅርቦት በሰፊው ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡
በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶች እርስ በእርስ በመተሳሰርና በመቀናጀት ህጋዊ በሆነ መንገድ በታማኝነት እና ግልጽ በሆነ አሰራር ስረዓት ውስጥ በማለፍና የተዘረጋውን ሲስተም በመጠቀም በገበያው ውስጥ ያለውን የእንስሳት መድኃኒት እጥረት ለመፍታትና ከሃገር አልፎ ለጎረቤት ሀገሮች ለማቅረብ መስራት አለባችሁ ሲሉ ዶ/ር ሀሚድ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ሀሚድ አክለውም በቀጣይ በባለስልጣኑ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና የአሰራር ሂደቱን ለማዘመንና ለማቅለል እንድሁም የተግልጋዮችን ድካምና እንግልት ለማስቀረት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁሉንም አገልግሎቶች በኦላይን እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
የአቢሲኒያ የእንስሳት መድኃኒት አስመጭና ጅምላ አካፋፈዮች ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ስለሽ መኮንን በእለቱ የተሰጠው ስልጠና በዘርፉ ለተሰማራነው አካላት በዋናነት አገልግሎት ለማግኘት ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የምናባክነውን ጊዜ የሚቆጥብና በተገልጋዩና አገልግሎት ሰጭው በኩል ግልጽ የሆነ አሰራር እንድኖር ይጠቅማል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መድኃኒት ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ በበኩላቸው መንግስት በአሁኑ ጊዜ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ስርዓት እንዲሆኑ አቅጣጫ ማስቀመጡን ተከትሎ የእንስሳት መድኃኒት ወጪ እና ገቢ ንግድ ስርዓትን በአንድ መስኮት አገልግሎት ላላፉት አምስት አመታት 5120 በላይ ማመልከቻዎች የቅድመ ማስገቢያ እና የመልቀቂያ ፈቃድ በአንድ መስኮት አገልግሎት መስጠት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡
ዶ/ር ሰለሞን ጨምረውም ሌሎች የእንስሳት መድሃኒት አገልግሎቶችን ለማዘመን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 5/በአምስት/ የእንስሳት መድሃኒት ምዝገባ የሰነድ ግምገማ በጥቅሉ 56 አገልግሎቶችን በኢ-ሰርቪስ ኦንላይን አገልገሎት እየሰጠን ነው በለዋል፡፡
በእለቱ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ሌሎች አስራ ሶስት (13) የእንስሳት መድኃኒት ሬጉላቶሪ አገልግሎቶችን በኢ-ሰርቪስ ለመጀመር መሆኑን በመጠቆም ከዚህ መድረክ በኋላ ሁሉንም አገልግሎቶች በኢ-ሰርቪስ ኦንላይን ብቻ እንደሚሰጡ ዶ/ር ሰለሞን ገልጸዋል ::
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234
በመንበረ ሀይሉ
——————————–
የማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድን ከመከላከልና መቆጣጠር አኳያ የሚዲያ አካላት ድርሻ ወሳኝ ነው፡፡
**********
/ቢሾፍቱ ፣ህዳር 5/2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/
መድረኩን የጤና ሚኒስቴር ፣ የግብርና ሚኒስቴር እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን ፣ የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡
በመድረኩ የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ ሲባል ምን ማለት ነው፣ እንዴት ይከሰታል እና የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ በሰዎች ፣ በእንሰሳትና በእጽዋት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት የሚል ጽሁፍ በባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል ፡፡
የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ መድሃኒቶችን በብዛት በመጠቀምና አላግባብ በመጠቀም የሚከሰት እንደሆነና ከሰው ወደ ሰው ፣ ከእንሰሳት ወደ ሰው እና ከአካባቢ ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዲሁም በጤና ፣ በኢኮኖሚ ፣በማህበራዊ ፣ በአካባቢና እጽዋት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ተጠናከረ የግንዛቤ ፈጠራ እና የመተላለፊያ መንገዶችን መሰረት ያደረገ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ መሰራት እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
የሚዲያ አካላት ከዚህ መድረክ በኋላ የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በበሽታ አምጭ ተህዋሲያን መለመድ እንደ ሀገር ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል እና አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን በውል በመረዳት፣ የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ እና የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በበሽታ አምጭ ረቂቅ ተህዋሲያን መለመድ ላይ ያለውን የግንዛቤና የአረዳድ ችግር ለመቅረፍ በተለያየ መንገድ መረጃዎችን በማሰራጨት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የዘረፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ: Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡ eaapr_1234
ባለስልጣኑ በሚያደርገው የቁጥጥር ስራ ላይ የህግ አካላት ድርሻ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡
****
(አዳማ ፣ህዳር 9/2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን )
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ለዐቃቢያንና የፖሊስ አባላት በተቋሙ ስልጣንና ተግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሃብታሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ስረዓት በመዘርጋት እና በመተግበር በአለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ ጎጅ ተጽዕኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ ለማስቻል ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣት ስራዎችን ሲሰራ የህግ ማዕቀፎችን፣ አዋጆችን ፣ መመሪያዎችንና ደንቦችን መሰረት አድርጎ ሲሆን ይህንን ለማሰፈጸም ደግሞ ከህግ አካላት ጋር ተግባብቶና ተናቦ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ለህግ አካላት የተቋሙን ስልጣንና ተግባር እንዲሁም አሰራሩ ምን እንደሚመስል ስልጠና በመስጠት ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግና ለስራችን ተባባሪ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለው፣ የስልጠናው ተሳታፊዎች በተፈጠረላቸው ግንዛቤ ለሚደረገው የቁጥጥር ስራ ተባባሪ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡
የህግ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አስመረት ተስፋይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ስልጣንና ተግባር በተመለከተ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል ፤ የቁጥጥር ተግባሩ እንደ ሀገር የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ በተመለከተ ከእንሰሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ዶ/ር ሀይሉ ዘሩ፣ ከእጽዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ አቶ አንማው ይሄነው እና በቁጥጥር ወቅት የታዩ የህግ ጥሰቶች እና ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊነትን በተመለከተ ከህግ አገልገሎት ስራ አስፈጻሚ ክፍል በወ/ሮ አምሳል ተፈራ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
የባለስልጣኑ የእንስሳት ምርትና ግብዓት የጥራት ምርመራ ማዕከል ሀላፊ ዶ/ር በላቸው ተፈራ በውይይቱ ላይ ለተነሱ ሀሳቦችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተው ባለስልጣን መ/ቤቱ በቀጣይ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የአሰራር ችግሮችን በመፍታትና የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የክትትልና ቁጥጥር ስራው በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ: Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡ eaapr_1234
ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፤
********
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማዕከላት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በአራቱ አቅጣጫ ለሚገኙ ማዕከላትና ጣቢያ ሀላፊዎች እንዲሁም ዴስክ ሀላፊዎች እስካሁን ባለስልጣኑ የሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ ውይይት አካሂዷል፡፡( ህዳር 26/2017 ዓም ) ኢ.ግ.ባ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ባለስልጣኑ በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀው በተለይም ተቋሙ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም በየተሰማራበት የስራ ድርሻ ላይ በሀላፊነትና በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ማዕከላት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር ገመዳ ቢነግዴ ባለስልጣኑ ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የማዕከላት አደረጃጀት፣ ተግባርና ሀላፊነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘው የባለስልጣኑ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሰረት አበባው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን አቅርበዋል፡፡
የባለስልጣኑ እንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ባለስልጣን መ/ቤቱ በሰራቸው ስራዎች ላይ ግልፅ የሆነ ግንዛቤን ለመፍጠር የተዘጋጀው መድረክ አስፈላጊና ቀጣይነት ያለው መሆኑን ገልፀው በተለይም እስካሁን በተሰሩ ስራዎች ላይ ጠንካራና ደካማ የሆኑት ተለይተው ለቀጣይ ስራዎች ውጤታማነት የተሻለ አሰራርን ለመፍጠር ያስችላሉ ብለዋል፡፡
የባለስልጣኑ እፅዋት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ግብርና ሪጉላቶሪ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም አካል በተሰማራበት የስራ ድርሻ በሀላፊነትና በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ምላሽ ሰጥተው በሂደት የሚፈቱትን ለቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ: Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡ eaapr_1234
በፀረ-ተባይ ኬሚካል ቁጥጥር ላይ አገር አቀፍ የውይይት መድረክ ተካሄደ፤
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ሪጉላቶሪ ከፌደራል ባለድርሻ አካለትና ከክልል ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ሀላፊዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ (ህዳር 26/2017 ዓም አዳማ) ኢ.ግ.ባ
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ዘርፍ ሪጉላቶሪ ም/ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን ደንብ ቁጥር 509/2022 እና አዋጅ ቁጥር 674/2010 መሰረት በማድረግ ባለስልጣኑ የፀረ- ተባይ ጥራት፣ ደህንነት እና ውጤታማነትን በማረጋገጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ግንዛቤን መፍጠር ሲሆን በተለይ ደግሞ የፀረ-ተባይ ኬሚካል ባግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋለ በሰው ልጅ፣ በአካባቢ፣ በእንስሳትና እና በዕፅዋት የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ሁሉም በሀላፊነትና በቅንጅት በሚሰራበት ሁኔታ ላይ ለመመካከር ነው ብለዋል፡፡
በባለስልጣኑ የፀረ- ተባይ እና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር በየነ ንጋቱ በአገር አቀፍ ደረጃ የፀረ- ተባይ ኬሚካሎች የቁጥጥር ስርዓትን በተመለከተ እና ከፀረ-ተባይ ጋር በተያያዘ እየደረሱ ያሉ የጤና ፣የአከባቢ እና የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከዚህ ጋር አያይዘውም ጥራቱን የጠበቀ የፀረ-ተባይ አቅርቦት፣ አጠቃቀም ፣ ቁጥጥር፣ ስርጭትና አወጋገድ እንዲኖር የፌደራል ባለድርሻ አካላትና የክልል ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት ስልጣንና ሀላፊነታቸውን በሚገባ ተረድተው በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የባለስልጣኑ የፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ ሪጉላቶሪ ዴስክ ሀላፊ አቶ ብርሀኑ በበኩላቸው ጊዜ ያለፈባቸው የፀረ-ተባይ ኬሚካሎች በአገራችን ያለውን ክምችት፣ ምን እንደሚመስል እና በሰውና በአካባቢ ላይ የሚያመጣውን ስጋት በተመለከተ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም ዶ/ር በየነ ንጋቱ በተሳታፊዎች የፀረ-ተባይ ቁጥጥርን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ምላሽ ሰጥተው በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሀገራዊ የፀረ-ተባይ ቁጥጥር የጋራ ስምምነት ረቂቅ ሰነድ ዝግጅት ስራ በባለስልጣኑ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ብርቱካን አዲሱ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ: Eaa Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡ eaapr_1234